ጥቅምት 22/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ እጅግ ቅንጡ የሆነውንና በዚህኛው ሞዴል 21ኛውን Airbus A350-900 (ET-BCE) አውሮፕላን መረከቡን አስታውቋል።
አየር መንገዱ ዛሬ ማለዳ የተረከበው ይህ ኤርባስ ኤ350-900 ሞዴል አውሮፕላን በመደበኛ ባለሦስት ክፍል አቀማመጥ ከ332 እስከ 352 መንገደኞችን ያስተናግዳል፡፡
እንዲሁም ከአጭር ርቀት እስከ ብዙ ርቀት በረራዎች 18 ሺሕ ኪሎ ሜትር በረራዎችን ሳያርፍ መብረር ይችላል፡፡
አየር መንገዱ "ለቅልጥፍና፣ ለምቾት እና ለዘላቂ የአቪዬሽን አመራር ያለንን ቁርጠኝነት ይበልጥ ያሳድጋል" ሲል አየር መንገዱ በማኅበራዊ የትስስር ገጹ ላይ ገልጿል፡፡
ይህ ዘመናዊ አውሮፕላን አየር መንገዱ ለሚሰጠው አገልግሎት ይበልጥ የሚያጠናክር እና በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ያለውን የመሪነት ሚና የሚያስቀጥል መሆኑንም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ማስፋፊያው አውሮፕላን ለማምረት እቅድ እንዳለው ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን፤ በመጪዎቹ ዓመታት የአውሮፕላን ክፍሎችን በቀጥታ ለቦይንግ ማቅረብ እቅድ መያዙን ገልጿል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 21ኛውን ኤርባስ A350-900 አውሮፕላን መቀበሉን አስታወቀ