መስከረም 22/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) አንጋፋዋ አርቲስትና ኮሜዲያን ፍሬሕይወት ባሕሩ ባጋጠማት ድንገተኛ ሕመም ምክንያት በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡
አርቲስት ፍሬሕይወት በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ዓለም ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያላት አንጋፋ ባለሙያ የነበረች ሲሆን፤ በተለይም የቀለጠው መንደር፣ ፎርፌ፣ ረመጥ፣ ነቃሸ በተሰኙ ታዋቂ ሥራዎችዋ አድናቆትን አትርፋለች ፡፡

ፍሬሕይወት ሥራዋን የጀመረችው በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በውዝዋዜና ዳንስ ሲሆን፤ የላቀ ችሎታዋን በመድረክ ካሳዩት አንጋፋ ከያኒያን መካከል ተጠቃሽ ነች፡፡
ከቲያትር በተጨማሪም በበርካታ ፊልሞችና የሙዚቃ ቪዲዮዎች ላይ የሰራች ሲሆን፤ በስራዋም በርካታ ዕውቅና እና ሽልማቶች ተበርክተውላታል።
የሀገር ፍቅር ቴአትር በአርቲስት ፍሬህይወት ባህሩ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን የገለጸ ሲሆን፤ ለወዳጅ ዘመዶችዋ እንዲሁም አድናቂዎችዋ መፅናናትን ተመኝቷል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ