በሀገር ደረጃ የተጀመረውን የኢኮኖሚ ቆጠራ ማደናቀፍ በፍፁም የተከለከለ ነው ሲል አዲስ አበባ ፕላንና ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ያሉ የንግድ ድርጅቶች ብዛትን ለማወቅ የሚረዳ ቆጠራ መካሄድ መጀመሩን የአዲስ አበባ ፕላንና ልማት ቢሮ በትላትናው ዕለት ገልጿል፡፡

Post image


ቆጠራው በመደበኛ ኢኮኖሚ እና መደበኛ ባልሆነ ኢኮኖሚ ያሉ ድርጅቶችን ለመለየት እንደሚረዳም ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ቀደምም የአዲስ አበባ ግንባታ ፍቃድ ባለስልጣን በከተማዋ የሚገኙ ሕንጻዎች ቆጠራ ማከናወኑ የሚታወስ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ካካሄደች ድፍን 21 ዓመት አልፏታል፡፡

የአዲስ አበባ ፕላንና ልማት ቢሮ የዚህ ቆጠራ ዋና አስፈላጊነት በከተማዋ ያሉ ድርጅቶች ብዛትን ለማወቅ መሆኑን ገልጿል፡፡ በተጨማሪም 'በወጪ ዜጋ ነው በሀገር ውስጥ ዜጎች የተያዙት?' የሚለዉን ለመለየት ነው ተብሏል።

ሌላው የድርጅቶችን መጠን መለየት በማስፈለጉ ነው የተባለ ሲሆን፤ ማለትም ከጥቃቅን አነስተኛ እስከ ከፍተኛ ድርጅት ያሉትን ለመለየት በማሰብ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በመደበኛ ኢኮኖሚ ውስጥ ነው ያሉት መደበኛ ባልሆነ ኢኮኖሚ የሚለውንም የሚለይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ ቆጠራ ከንግድ ቤቶቹ በተጨማሪ በሥራቸው ያሉ ሠራተኞች ብዛትንም ጨምሮ የሚቆጥር መሆኑም ተነስቷል፡፡

የቆጠራው ዓላማም የሀገሪቱን ምርት መጠን (GDP) ለመለየት የሚረዳ መሆኑን ተገልጿል፡፡

አድስ አበባ ለሀገር ውስጥ ምርት ያላትን አስተዋፅኦ ለመለካት የሚረዳ መሆኑም በትላትናው ዕለት ቢሮው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የሀርን ኢኮኖሚ ከዓለም ኢኮኖሚ ጋር ለማነፃፀርና ደረጃውን ለማወቅ ብሎም የውጭ ኢንቨሰትመንትን ለመሳብ ይህ ቆጠራ የሚረዳ መሆኑን የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ ገልጸዋል፡፡

Post image

ሁሉም ዜጎችና የንግዱ ማኅበረሰብ የሚሰበሰበው መረጃ ለሀገር የሚጠቅም መሆኑን በመረዳት መረጃውን በመስጠትና በጎ ትብብር በማድረግ እንዲያግዙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ነገር ግን ይህ ቆጠራ በሚከናወንበት ወቅት ህብረተሰቡ ትብብር ማድረግ እንዳለበት የገለጹ ሲሆን፤ ይህንን ቆጠራ ማደናቀፍ በፍፁም የተከለከለ ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ቆጠራው የሚካሄደው የፕላንና ልማት ቢሮ ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ጋር በመተባበር መሆኑም ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ በጋዜጣዊ መግለጫው፤ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራው ጥናት ጠቃሚ የመረጃ ግብዓት በማስገኘት በኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ያለው አበርክቶ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህንንም ሥራ ከወረዳ እስከ ክፍለከተማ በማዋቅር መሠርት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

19 የሚሆኑ ንግድ ዓይነቶች መኖራቸውን ያነሱ ሲሆን፤ ከሰፈር ውስጥ ሻይ ቡና አስከ አምስት ኮከብ ሆቴል ድረስ በዚህ ቆጠራ ውስጥ እንደሚያልፉ አቶ አደም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የቢዝነስ ስታቲስቲክስ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ናቃቸው ነጋሽ በበኩላቸው፤ ቆጠራው የተጀመረው ጥቅምት 1 ነው ይላሉ፡፡

Post image

ላለፉት 25 ቀናትም በመላ ሀገሪቱ በ56 የስልጠና ማዕከላት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ስልጠና ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

ይህ ቆጠራም በመላው ሀገሪቱ የሚካሄድ መሆኑን የገለፁ ሲሆን፤ በአዲሰ አበባ ከዋና ዋና ድርጅቶች ጀምሮ ይካሄዳል ብለዋል፡፡

ይህ ቆጠራ ሁሉንም ህበረተሰብ የሚጠቅም መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ያሉት መሪ ሥራ አስፈጻሚው፤ ለንግድ ተቋማቱም ደጋፍ የሚያሰጥ መሆኑም አንስተዋል፡፡

ይህን ቆጠራ የሚያካሄደው ኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በበኩሉ ለቆጠራው የሚሆኑ 5 ሺሕ 500 በላይ ባለሙያዎች መሰማራታቸውን ገልጿል፡፡

Post image

እነዚህ ባለሙያዎችም ከቤት ቤት በመዘዋወር ቆጠራውን የሚከናውኑ መሆናቸውንም አስረድቷል፡፡

ቆጠራው በዋናነት መደበኛ እና መደበኛ ያልሆኑ ንግዶች የሚዳሰሱ መሆኑም ተቋሞቹ ገልጸዋል፡፡

በዚህም ቤታቸው ውስጥም ሆነ ከቤት ውጪ የሚሰሩ የንግድ ተቋማትን ጨምሮ በኦንላይን ንግድ አየር በአየር የሚነግዱትን ጭምር የሚያጠቃልል መሆኑን ተነስቷል፡፡

ባለሙያዎቹም ጥያቄያቸውን በዚህ መሠረት በማዘጋጀት ቤት ለቤት በመሄድ የሚደረግ መሆኑም ነው አቶ ናቃቸው የሚገልጹት፡፡

የኢንዱስትሪና የከተማ ግብርና የኢኮኖሚ ዘርፎች ለአጠቃላይ የሀገር ምጣኔ ሀብት ያላቸውን አበርክትዎ ለማወቅ የሚረዳ መሆኑም ተነስቷል፡፡

የዘርፎች የተናጠል ድርሻን ወቅታዊ ለማድረግ የሚረዳ ስታቲስቲካላዊ መረጃ ለማግኘት ብሎም በቀጣይነት ለሚከናወኑ ዘርፈ ብዙ ጥናቶችና ለፖሊሲዎች ግብዓት የሚሆን የተሟላ መረጃ ለማግኘት እንደሚረዳም ከተነሱት ሃሳቦች መካከል ይገኝበታል፡፡

የሚጀመሪያው ዙር በ45 ቀናት ውስጥ የሚጠነናቀቅ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ እስከ የካቲት 30 ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ እንሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

በዚህም በ19ም ተቋማት የት እንዳሉና የመለዩት ሥራ ከተሰራ በኃለ የቆጠራው ሥራ እንደሚከናወንም አቶ ናቃቸው አንስተዋል፡፡

ይህ ኢኮኖሚ ቆጠራም በመላው ሀገሪቱ እየተከናወነ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፤ ቆጠራውም በኢኮኖሚው ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚረዳ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡

ከዚህ ቀደምም የአዲስ አበባ ግንባታ ፍቃድ ባለስልጣን በከተማዋ የሚገኙ ሕንጻዎች ቆጠራ ማከናወኑ የሚታወስ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ካካሄደች ድፍን 21 ዓመት አልፏታል፡፡

ቆጠራውን ከ2010 እስከ 2014 ድረስ ለማካሄድ የተሞከረ ቢሆንም፤ በተደጋጋሚ ጊዜ እየተራዘመ አሁንም ድረስ ሳይካሄድ ቆይቷል፡፡

‎#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ