መስከረም 19/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአቃቂ ቃልቲ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ሥሙ ቦቼ ሰፈር አካባቢ በኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ ስር አዋሽ የቆዳ ፋብሪካ የተሰኘ ድርጅት፤ ከፋብሪካው የመነጨ በካይ የፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝ በመልቀቁ 800 ሺሕ ብር መቀጣቱን አስታውቋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 06 ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ደሳለኝ ሌንጮ እንደገለፁት፤ ድርጅቱ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ የደንብ መተላለፍ ፈፅሞ 400 ሺሕ ብር ተቀጥቶ ነበር፡፡

Post image

ዳግመኛም ከጥፋቱ ሳይታረም ለሁለተኛ ጊዜ ያመነጨውን በካይ ፈሳሽ ቆሻሻውን በድጋሚ ጨለማን ተገን አድርጎ ወደ ወንዝ ሲለቅ በደረሰ የማህበረሰብ ጥቆማ መሠረት በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ በተቀመጠው የቅጣት አወሳሰድ እርምጃ በተደጋጋሚ ጥፋት አጥፊ ሆኖ 800 ሺሕ ብር መቀጣቱ ተገልጿል።

Post image

ኃላፊው አክለውም ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት መድቦ የወንዝ ዳርቻ የልማት ሥራዎችን እየሰራ ባለበት ወቅት እንደዚህ አይነት ተግባር መፈፀም ተገቢ አለመሆኑን ገልጸው፤ ሌሎች ተቋማት ሆኑ ግለሰቦች ከዚህ እርምጃ መማር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ