የካቲት 8/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ-መንበርነትን በ2024 ስትመራ የነበረችው ሞሪታኒያ ስልጣኑን ለአንጎላ አስረክባለች።
38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ላይ ይገኛል።
በጉባዔው መክፈቻ ላይ የሕብረቱ ሊቀመንበር የነበሩት የሞሪታኒያው ፕሬዝዳንት ሞሃምድ ኡልድ ጋዝዋኒ ለወቅቱ የሕብረቱ ሊቀ-መንበር ሆነው ለተመረጡት የአንጎላ ፕሬዝዳንት ዧ ማኑኤል ጎሳዌስ ሎሬንሶ ሊቀመንበርነቱን አስረክበዋል።
የሞሪታኒያው ፕሬዝዳንት ለአንጎላው አቻቸው መልካም የሥራ ዘመን ተመኝተዋል።
በዚህም መሰረት አንጎላ የ2025 የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ-መንበር በመሆን ሥራዋን የምትጀምር ይሆናል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
የ2025 የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ-መንበርነትን አንጎላ ተረከበች
