ጥር 3/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ Stragle to save Ethiopian Jewary የተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፤ በ672 ሚሊየን ብር ወጪ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትና የቤተ-እስራኤላውያን ሙዚየም ሊገነባ መሆኑ ተገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው ድርጅቱ በተገለጸው ወጪ በከተማዋ የማህበራዊ ተቋማትን ለመገንባት መስማማቱን ገልጸዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ለሁለቱ ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ የሚውል 50 ሺሕ ካሬ ሜትር መሬት የመስሪያ ቦታ ለመስጠት መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
በስምምነት ስነ-ስርዓቱ ላይም በድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስተር ጆ ፋይት ተገኝተዋል፡፡
ለማህበራዊ ተቋማቱ የግንባታ የገንዘብ ድጋፍ የተገኘው የአሜሪካን ጅውሽ ማህበረሰብ ከተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መሆኑ በስምምነቱ ላይ መመላከቱን ከክልሉ ኮምዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡