ሕዳር 23/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታ የኬንያ አቻውን 3 ለ 0 በማሸነፍ ከ22 ዓመታት በኃላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ተመልሷል።
በዚህም ዛሬ የሴካፋ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታ የኬንያ አቻውን የኢትዮጵያ ከ17 ዓመታ በታች ብሔራዊ ቡድን 3 ለ 0 በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
ለመጨረሻ ጊዜ በ1997 በስዋዚላንድ በተዘጋጀው ውድድር የተሳተፈችው ኢትዮጵያ የዛሬውን ውጤት ተከትሎ፤ ከ22 ዓመታት በኋላ ወደ አህጉራዊ ውድድር ተመልሳለች።

በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ብሔራዊ ቡድን ከኬንያ ጋር ባደረገው ጨዋታ የማለፊያ ግቦቹን ዳዊት ካሳው፣ ቢኒያም አብረሀ እና ብሩክ እይላቸው አስቆጥረዋል።
ከ17 ዓመታ በታች ብሔራዊ ቡድኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ የተደረገው የ”ሮድ 2029” ፕሮጀክት አካል እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ