ሕዳር 25/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የአህጉሩ ትልቁ ውድድር የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አዘጋጅንት ሊጀመር 17 ቀናት ብቻ የቀሩት ሲሆን፤ ውድድሩ ከታሕሳሰ 12 እሰከ ጥር 9 በሞሮኮ ይደረጋል።
ከውድድሩ አሰቀድሞ ግን አምስት ሀገራት አሰልጣኞቻቹውን ማሰናበታቸው ብዙሃንን እያስገረመ ይገኛል።
አሰልጣኟን ያባረረች የመጀመሪያዋ ሀገር አንጎል ስትሆን፤ ሀገሪቱ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ፔድሮ ጎንካልቭሰን በመሰከረም ወር ላይ ባስመዘገቡት ደካማ ውጤት እና በቻን 2024 ውጤት አልባ ጉዞ ካደረጉ በኋላ ተሰናብተዋል።

ሌላኛዋ አሰልጣኟን ያሰናበተች ሀገር ዙምባቡዌ ናት፡፡ ዙምባቡዌ ከጀርመናዊው ታክቲሻያን ማይክል ኔሰ ጋር ተለያይቶዋል፡፡ ምክንያቷው ደግሞ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ባደረጉት ደካማ ጉዞ በኋላ በጥቅምት ወር መጨረሻ ከኃላፊነታቸው እንዲሰናበቱ ሆኖል።

ሦሰተኛዋ አሰልጣኝዋን ያሰናበተች ሀገር ደግሞ ታንዛንያ ሰትሆን፤ አሰልጣኝ ሄሜድ ሱሌመንን የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀመር ከወር ያንሰ ጊዜ ሲቀረው ማሰናበቷ አሰድንጋጭ ነበር፡፡ ታንዛንያ በአፍሪካ ዋንጫ በምድብ ሦሰት ከዩጋንዳ፣ ከናይጄሪያ እና ከቱንዚያ ጋር ተመድባለች።

እንዲሁም ዛምቢያም ከአሰልጣኟ ጋር የተለያየች ሀገር ሆናለች፡፡ የዛምቢያ አሰልጣኝ አቭራም ግራንት በጥቅምት ወር ላይ የተሰናበቱ ሲሆን፤ ለሰንብታቸው መንስኤ ደግሞ በቻን ዋንጫ ባስመዘገቡት ደካማ ውጤት እና ለ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በምድቧ ሦሰተኛ ሆና በመጨረሷ ነው ተብሏል።

የመጨረሻዋ አሰልጣኝ አሰናባች ሀገር በሳሙኤል ኤቶ ፕሬዝዳንትንት የምትመራዋ ካሜሮን ናት፡፡ የማይበገሩት አንበሶቹ ቤልጄማዊው አሰልጣኝ ማርክ ብሪስ ካሜሮንን ለዓለም ዋንጫ ባለማሳለፋቸው መሰናበታቸው ተገልጿል።

ካሜሮን በአፍሪካ ዋንጫ በምድብ ስድሰት ከጋቦን፣ ከአይቮሪኮሰት እና ሞዛንቢክ ጋር ተመድባለች።
የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አሰተናጋጅነት ከ17 ቀናት በኋላ ታሕሳሰ 12 ቀን 2018 ይጀመራል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ