ታሕሳስ 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከአዲሱ ዓመት 2025 ጀምሮ በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ሀገራት ዜጎች ያለ ቪዛ ወደ ሀገሯ እንዲገቡ መፍቀዷ ተሰምቷል።

ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ በአፍሪካ ውስጥ ላሉ ሁሉም ሀገራት ዜጎች ከቪዛ ነፃ እንዲገቡ መፈቀዱ በመላው አፍሪካ ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን መናገራቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

አዲሱ አካሄድ ቱሪዝምን፣ ንግድን እና ወደ ምዕራብ አፍሪካ ሀገር ጉዞን እንደሚያሳድግ ተስፋ የተደረገበት ሲሆን፤ ተንታኞች ቀደም ሲል የቪዛ እገዳ ለእነዚህ ዘርፎች እንቅፋት እንደሆነ ሲገልፁ ነበር።

ውሳኔው ጋናን ከአህጉሪቱ የአፍሪካ ፓስፖርት ከፈቀዱ አምስተኛዋ ያደርጋታል። ሩዋንዳ፣ ሲሸልስ፣ ጋምቢያ እና ቤኒን ተመሳሳይ ፖሊሲ አላቸው።