የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ኮሚሽኑ ሥራውን ሲጀምር አብሯቸው ለመስራት ከመረጣቸው አምስት አካላቱ አንዱ ፓለቲካ ፓርቲዎች መሆኑን ገልጸዋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር የጋራ ምክር ቤቱ ሌሎች ከመጀመሪያው ጀምሮ የኮሚሽኑን ሥራ ያልተቀበሉትን ወደ ኮሚሽኑ እንዲመጡ ጠይቀዋል።
የጋራ ምክር ቤቱን ወክለው የተገኙት የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ፤ ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ ከፓርቲዎች የሰበሰበውን ወደ 7 የሚሆኑ አጀንዳዎችን ያሰረከበ ሲሆን፤ በተለይም በሀገረ መንግሥት ምሰረታ፣ በታሪክ ትርክት፣ የውጭ ግንኙነቶችን ጨምሮ 64 ንዑስ አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረክቧል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተለያዩ አካላት አጀንዳዎች የመሰብሰብ ሥራውን በመቀጠል በ9 ክልሎችና 2 ከተማ አስተዳደሮችን ሥራዎችን ማጠናቀቁም ተገልጿል።
የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7 የሚሆኑ አጀንዳዎቹን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከበ
ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከተለያዩ ፓርቲዎች የሰበሰበውን ወደ 7 የሚሆኑ ዋና አጀንዳዎችንና 64 የሚሆኑ ንዑስ አጀንዳዎችን ሰብስቦ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክቧል።