መቀመጫውን በቨርጂኒያ አርሊንግተን ያደረገውና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የማማከር፣ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ ማቅረብ ላይ የሚሰራው ሚለር ፎር ኒውትሬሽን፤ በኢትዮጵያ በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።
የሚለር ፎር ኒውትሬሽን ኢትዮጵያ ፕሮግራም ማናጀር ኢያቄም አምሳሉ፤ ይህን ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥትና የኢንዱስትሪው ዘርፍ ጋር ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል።
"የንጥረ ነገር እጥረት ችግር ለቤተሰብ፣ ለማህበረሰብ ከፍ ሲልም ለሀገር ትልቅ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው" ያሉም ሲሆን፤ በዚህ የተጎዳው ማህበረሰብ ለአንድ ሀገር ያበረክት የነበረው አስተዋፅዖ ቀላል አለመሆኑን ጠቁመዋል።
ለዚህም የስንዴ ዱቄት በበርካታ የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ ጥቅም ላይ የሚውል በመሆኑ፤ ከ25 እስከ 30 በመቶ የስንዴ ዱቄት አምራች ፋብሪካዎች የበለፀገ (fortified) ዱቄት እንዲያመርቱ ግብዓትና ማሽኖች መግዛታቸውን ተናግረዋል።
እንዲሁም ሚለር ፎር ኒውትሬሽን በጀመረው እንቅስቃሴ በሦስት ወራት ውስጥ እስከ 60 በመቶ ለሚሆኑ የስንዴ ዱቄት አምራቶች አስፈላጊውን የግብዓትና ማሽን ድጋፍ ለማድረግ እቅድ መያዙን ጠቁመዋል።
በተመሳሳይም 38 የሚሆኑ ማጣሪያ ያላቸው የዘይት ፋብሪካዎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ማሟላላታቸውን ገልጸዋል።
የንጥረ ነገር እጥረት ምክንያት 30 በመቶ የሚሆነው የአለም ሕዝብ አካላዊና አዕምራዊ አቅሙን እንዳይጠቀም ማድረጉን ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ።
ኢትዮጵያ በምግብ ንጥረ ነገሮች እጥረት ምክንያት በዓመት 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚታጣ ተገለጸ
ሕዳር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ የንጥረ ነገር እጥረት በጤና ላይ የሚያስከትለውን ችግር ለማከም እና ለመርዳት ብቻ፤ በዓመት ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ 5 ቢሊየን ዶላር እንደምታጣ ሚለር ፎር ኒውትሬሽን ኢትዮጵያ ገለጸ።
![ኢትዮጵያ በምግብ ንጥረ ነገሮች እጥረት ምክንያት በዓመት 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚታጣ ተገለጸ](/_image?href=https%3A%2F%2Fcdn.sanity.io%2Fimages%2Fbede4k7t%2Fproduction%2Fbf3326f3051406f2c0c5fa1260cca0effd39b0d1-1080x701.jpg&w=1080&h=701&f=webp)